ዱቤ ለዛሬ አለ! የአፖሎ ማይክሮሎን ወደ 100,000 ብር አደገ!

የፋይናንሱ ዘርፍ በቋሚነት በመዘመን ላይ በሚገኘው የቴክኖሎጂ ዕድገት በመደገፍ አዳዲስ አማራጮችን በማስተዋወቅና በማላመድ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በኅብረተሰቡ የዕለት ከዕለት ኑሮ አኳያ ጊዜን በቆጠበና ምቾትን በጠበቀ አኳኋን አስቻይ የሆኑ ዘርፈ-ብዙ ዕድሎች በተከታታይ በመመቻቸት ላይ ናቸው፡፡

 በእዚሁ ረገድ አቢሲንያ ባንክ በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ በሚሠሩ ወርኃዊ ደመወዝ ተከፋዮችን ትኩረት ያደረገ አዲስ የአፖሎ ብድር መተግበሪያን ሥራ ላይ አውሏል፡፡ በአዲሱ የአቢሲንያ ባንክ የአፖሎ ብድር መተግበሪያው አማካኝነት ለወርኃዊ ደመወዝተኞች እስከ ብር100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት አዲስ ዕድልን ተፈጥሯል፡፡ በመተግበሪያው አማካኝነት ዕለታዊ የባንክ ተግባራት ያካተታቸው ወደ ቅርንጫፎች መሄድ ሳያስፈልግ አዲስ የባንክ ሒሳብ መክፈት፣ፈጣን እና ምቹ የገንዘብ መላላኪያ መንገድ(QR Code) ማካሄድ እና የመሳሰሉትን በተጨማሪ በማካተት ያከናውናል፡፡

በእዚህ አጭር ማብራርያ የአቢሲንያ ባንክ ሠራተኞች እና በአጋር ተቋማት ውስጥ በሚሠሩ (ወርኃዊ ደመወዛቸውን በአቢሲንያ ባንክ የሚቀበሉ) ሠራተኞች ከአፖሎ ሲበደሩ የሚያገኟቸውን ጥቅሞች፣ ከአፖሎ ብድር ለማግኘት መሟላት የሚኖርባቸው ጉዳዮች ብሎም አዲሱን የብድር አማራጭ በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችሉ መረጃዎች ይቀርባሉ፡፡   

ብድር በአፖሎ

አነስተኛ ብድሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተፈላጊነታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣና ካለ መያዣ የሚሰጡ የአጭር ጊዜ ብድሮች ሲሆኑ ዋና ተጠቃሚዎቹ ጥቃቅን የንግድ ሥራ አንቀሳቃሾችና ወርኃዊ ደመወዝተኞች ናቸው፡፡ ብድሮቹም በአብዛኛው የፍጆታ ዕቃዎች ወጭን ለመሸፈን ላይ እንደሚውል ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ 

የአፖሎ ብድር አገልግሎት የአነስተኛ ብድሮች ፍላጎትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፈጣን እና ምቹ የሆነ የብድር ታሪክ የመሰነጃ አሠራር (ደንበኞችን በብድር አመላለስ ደረጃቸው በሚገባ በመመደብ) መሠረት ቀልጣፋ እና አበረታች የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትን አሠራር አስተዋውቋል፡፡

አነስተኛ ብድሮች ለሁሉም የአፖሎ መተግበሪያ ተመዝጋቢ ተጠቃሚዎች ተደራሽ ቢሆኑም ለወርኃዊ ደመወዝተኞች አፈጻጸሙ ምቹ ሆኖ ይገኛል፡፡  የአፖሎ የአነስተኛ ብድር አገልግሎትን ለመጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም አዲስ ደንበኛ መተግበሪያውን በእጅ ስልኩ ከመጫን ባለፈ የባንኩ ዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትን ለማግኘት በመተግበሪያው ላይ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡

 ለአፖሎ ተጠቃሚዎች እና ከዚህ ቀደም ወርኃዊ ደመወዝን በቅድሚያ በብድር መልክ ከመተግበሪያው ስትወስዱ ለነበራችሁ ሠራተኞችን ሳይጨምር ለአዲሶች ቀጥሎ የተዘረዘሩት ጉዳዬች መሟላት ይኖርባቸዋል፡-

1-     መሠረታዊ መረጃዎች ያስገቡ

  • ለመተግበሪያው አዲስ ከሆኑ ለአገልግሎት አሰጣጥ ጠቃሚ መሆናቸው የታመነባቸው መረጃዎችን  በመጠይቁ መሠረት በጥንቃቄ መሞላት ይኖርበታል
  • ወርኃዊ ደመወዝተኞችን በተመለከተ የቅጥር ደብዳቤ እና የሥራ ፈቃድ መቅረብ ይኖርበታል

2-     መታወቂያ

ኢትዮጵያዊ ከሆኑ የነዋሪነት መታወቂያ ወይንም የብሔራዊ መታወቂያን ከመጠይቁ ጋር በተዘጋጀው ቦታ መያያዝ ይኖርበታል

3-     ለውጭ ሀገር ዜጋ

ፓስፖርት፣ ቪዛ ወይም  የመኖሪያ ፈቃድ(የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈ)   

4-     የመልዕክት አድራሻ

ከመሠረታዊ መረጃዎች በተጨማሪ  የስልክ እና የኢሜይል አድራሻዎች ለመረጃ ማረጋገጫ እና ለኢንፎርሜሽን ልውውጥ ይረዳ ዘንድ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡

5-     የባዮሜትሪክ መለያዎችዎን ያስገቡ

የፋይናንስ ደህንነትን ለማዘመን እና አስተማማኝ ለማድረግ ሲባል የአፖሎ መተግበሪያ እንደ የፊት ገጽ(Facial Recognition) እና የጣት አሻራን በስልክ ላይ በሚገኘው ካሜራ እና የአሻራ መቀበያ አማካኝነት መግባት ይኖርባቸዋል፡፡

ከላይ የተመለከቱትን መሠረታዊ መረጃዎች ገቢ ሲደረጉ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውል(One-time pin-OTP) የይለፍ ቃል ይላካል፡፡ ይህ ኮድ ሲገባ የአፖሎን የዲጅታል ባንኪንግ ዓለም መቀላቀል የሚያስችል ሒሳብ ከ10 ደቂቃ ባነሰ ጊዜና በተፈለገበት ቦታ ሆኖ መክፈት ያስችላል፡፡

መሠረታዊ ነጥቦች በተሻሻለው የአፖሎ መተግበሪያ ምን ብድር ብቁ ያደርጋል?

የአፖሎ ሒሳብ መኖር የመጀመሪያውና መሠረታዊው ጉዳይ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በመተግበሪያው ላይ የተመዘገቡ እና ወርኃዊ ደመወዝን በአቢሲንያ ባንክ የሚቀበሉ ከሆነ የአፖሎ መተግበሪያን አሁኑኑ ይከፈቱ፣

መተግበሪያው ከሌልዎት ለብድር ጥያቄዎ ያስፈልጋልና ከፕሌይ ስቶር/ አፕ ስቶር(Play Store/up store) በማውረድ ከላይ የተመለከቱትን ቀላል እና ፈጣን የመመዝገቢያ ቅደም ተከተሎች አንጻር ይመዝገቡ፡፡                                                                                                     በመቀጠል የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ ይበሉ፡-

  • መተግበሪያውን ሲከፍቱ ሒሳብዎ ጊዜያዊ አለመሆኑን ያረጋግጡ
  • የብድር አገልግሎት ጥያቄ ለማቅረብ ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ቢያንስ ለ6 ወራት የቆየ ደንበኝነት ሊኖርዎ ይገባል
  • ላለፈው አንድ ዓመት በአፖሎ መተግበሪያ የወሰዷቸውን ብድሮች መመለስዎን ያረጋግጡ!
  • ከዚህ ቀደም የወሰዱትን ብድር በወቅቱ ባለመመለስ ‘በልዩ ሁኔታ ክትትል የሚደረግባቸው ብድሮች’ ውስጥ በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ አለመመደቡን ያረጋግጡ፤ ይህንንም በቀላሉ በመተግበሪያዎት የሚላኩ መልዕክቶች ወይንም የስልክዎን የመልዕክት ማጠራቀሚያ (inbox) በመመልከት ለመለየት ይችላሉ፡፡

                   ለብድር ማመልከት የሚቻለው እንዴት ነው?

አንዴ ሒሳብዎን ከከፈቱ በኋላ ቀላል እና አጭር ቅደም ተከተሎችን ይከተሉ እነርሱም፡-

  • የቁጠባ ሒሳብዎ ጊዜያዊ አለመሆኑን ያረጋግጡ
  • ብድሮችን የተመለከተው ክፍል ሥር ‘የደመወዝ ብድር’ የሚለውን አማራጭ ይጫኑ
  • የብድር መጠይቁን ይሙሉ

ለብድር ጥያቄዎ ምላሽ 24 ሠዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መልስ ይደርስዎታል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የተጠየቀው የብድር ገንዘብ በአፖሎ መተግበሪያ ላይ በሚገኘው የዲጅታል ዋሌት ሒሳብ ገቢ ይደረግልዎታል (የብድር ጥያቄዎ ስለ መፈቀዱ ምላሽ አግኝተው ከተጠቀሰው ጊዜ ከዘገየ በመተግበሪያው ላይ ወደተመለከተው የጥሪ ማዕከል ይደውሉ)፡፡

                                 ምንያህል ብድር መውሰድ ይቻላል?

በአዲሱ የአፖሎ መተግበሪያ የደመወዝ ቅድመ ብድር አሠራር መሠረት አምስት የብድር ዑደቶች (loan cycles) ያሉ ሲሆን እነርሱም ‘የአቢሲንያ ባንክ ሠራተኞች’ እና ‘በባንኩ በኩል ወርኃዊ ደመወዛቸውን የሚቀበሉ ደንበኞች’ በሚል በሁለት መንገድ ተካተዋል፡፡

·                      ለአቢሲንያ ባንክ ሠራተኞች

የባንኩ ሠራተኛ ለሆኑ እና ወርኃዊ ደመወዛቸውን በቅድሚያ ለሚበደሩ ሠራተኞቹ በአዲሱ የአፖሎ  መተግበሪያ መሠረት ብድር የሚያገኙበት አግባብ በሦስት የብድር ማዕቀፎች (loan cycles) በመከፋፈል እንደሚከተለው ተቀምጧል፡-

1-     የመጀመሪያ ጊዜ ወይንም የመጀመሪያ ብድሩን በአግባቡ የከፈለ ተበዳሪ የባንኩ ሠራተኛ የጥቅል ወርኃዊ ደመወዙን (ከታክስ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት) 50%(አምሳ ከመቶ) ወይንም እስከ ብር 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር) ድረስ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡

2-     ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን ሁለት ብድሮች በአግባቡ ለከፈለ ተበዳሪ የባንኩ ሠራተኛ የጥቅል ወርኃዊ ደመወዙን (ከታክስ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት) 75%(ሰባ አምስት ከመቶ) ወይንም እስከ ብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) ድረስ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡

3-     ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን ሦስት ብድሮች በአግባቡ ለከፈለ ተበዳሪ የባንኩ ሠራተኛ የጥቅል ወርኃዊ ደመወዙን (ከታክስ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት) 100%(መቶ ከመቶ) ወይንም እስከ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ድረስ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡

·        በአቢሲንያ ባንክ በኩል ወርኃዊ ደመወዛቸውን ለሚቀበሉ ደንበኞች

ወርኃዊ ደመወዛቸውን በአቢሲንያ ባንክ በኩል ለሚቀበሉ ደንበኞች የጥቅል/ያልተጣራ ደመወዛቸውን (Gross Salary) እና የብድር አመላለስ ታሪካቸውን መሠረት መነሻ ጥቅል ደመወዛቸው 15%(አስራ አምስት ከመቶ) ወይንም ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በማድረግ እስከ ያልተጣራ ሙሉ(100%) ወርኃዊ ደመወዝ ወይንም ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ድረስ ለመበደር የሚያስችል አዲስ እና ቀልጣፋ አሠራርን እንደሚከተለው አቅርቧል፡-

1-     የመጀመሪያ ጊዜ ተበዳሪ፡ ይህም ተበዳሪው የደምወዙን (የታክስ እና የጡረታ መዋጮን ሳይቀንስ) 15% ድረስ መበደር ሲችል ይህም የብድር ጣሪያው ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ይሆናል

2-     የመጀመሪያ ብድሩን ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ያጠናቀቀ/ በሚገባ በመክፈል ላይ የሚገኝ ተበዳሪ፡ ይህም ተበዳሪው የደመወዙን (የታክስ እና የጡረታ መዋጮን ሳይቀንስ) 20%(ሃያ ከመቶ) ድረስ መበደር ሲችል ይህም የብድር ጣሪያው ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ይሆናል፡፡

3-     ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን ሁለት ተከታታይ ብድሮች በአግባቡ የከፈለ ተበዳሪ፡ ተበዳሪው የደመወዙን (የታክስ እና የጡረታ መዋጮን ሳይቀንስ) 25%(ሃያ አምስት ከመቶ) ድረስ መበደር ሲችል  የብድር ጣሪያው ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ይሆናል፡፡

4-     ከዚህ ቀድም የወሰዳቸውን ሦስት ተከታታይ ብድሮች በአግባቡ የከፈለ ተበዳሪ፡ ተበዳሪው የደመወዙን (የታክስ እና የጡረታ መዋጮን ሳይቀንስ) 35%(ሠላሳ አምስት ከመቶ) ድረስ መበደር ሲችል የብድር ጣሪያውን ማለትም ብር 35,000 (ሠላሳ አምስት ሺህ ብር) መበደር የሚችል ይሆናል፡፡

5-     ከዚህ ቀድም የወሰዳቸውን አራት ተከታታይ ብድሮች በአግባቡ የከፈለ ተበዳሪ፡ ተበዳሪው የደመወዙን (የታክስ እና የጡረታ መዋጮን ሳይቀንስ) 50%(አምሳ ከመቶ) ድረስ መበደር ሲችል ይህም የብድር ጣሪያው ብር 50,000 (አምሳ ሺህ ብር) ለመበደር የሚችል ይሆናል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ ተበዳሪው ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን ብድሮች እንደሚመልስበት አግባብ እየታየ የወርኃዊ ደመወዙን 100%(መቶ ከመቶ) ወይንም ከብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ያልበለጠ ገንዘብ ለመውሰድ ይችላል፡፡

                                     የብድር ወለድ ምጣኔው ምን ያህል ነው

በአቢሲንያ ባንክ አፖሎ መተግበሪያ የሚሰጡ ብድሮችን በተመለከተ እንደ ብድር መመለሻ ጊዜው የሚለያይ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል፤ በዚህም መሠረት፡-

ሳምንታዊ ብድር፡ በሣምንት ለመመለስ የተወሰደ የብድር ገንዘብ 2%(ሁለት ከመቶ) የአገልግሎት ክፍያ ከጠቅላላ የብድር ተመላሽ ገንዘብ በተጨማሪነት ይከፈላል፡፡

ወርኃዊ ብድር፡  የጠቅላላ ብድሩ 4%(አራት ከመቶ) የአገልግሎት ክፍያ ከጠቅላላ ተመላሽ ብድር  በተጨማሪነት ይከፈላል፡፡

የሩብ ዓመት/3 ወሩ የሚመለስ ብድር፡  የጠቅላላ ብድሩ 10%(አስር ከመቶ) የአገልግሎት ክፍያ ከጠቅላላ ተመላሽ ብድር ላይ በተጨማሪነት ይከፈላል፡፡

ዘግይተው የተከፈሉ ወይም የሚከፈሉ ክፍያዎች ላይ የሚጣል ቅጣት፡ ከአፖሎ መተግበሪያ ላይ ተወስደው በጊዜ ያልተከፈሉ ብድሮችን በተመለከተ ተበዳሪው ባልከፈለው ቀሪ ዕዳ ላይ በየወሩ የሚታሰብ 3.5% ቅጣት የሚከፍል ይሆናል፡፡  

 አፖሎ ከሌሎች መሰል መተግበሪያዎች በምን ይለያል?

በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተለያዩ የፋይናንስ እና የፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ድርጅቶች በሥራ ላይ የዋሉ በርካታ መተግበሪያዎች ይገኛሉ፤ ታድያ አፖሎ ለምን ለምን ጨዋታ ቀያሪ ነው ሊባል ቻለ?                                  

                                                አፖሎ የአነስተኛ ብድር   

Pበፈለጉት ቦታ በፈለጉት ጊዜ፡  የአፖሎን መተግበሪያ አንዴ ካወረዱና ከተመዘገቡ በኋላ ለ 24 ሠዓታት ለ7 ቀናት በአስተማማኝነት ያልተቋረጠ የብድር አገልግሎትን ያገኛሉ፡፡

Pደህንነትዎ በበቂ ሁኔታ ይጠበቃል፡ አዲሱ የአፖሎ መተግበሪያ የደንበኞችን የፋይናንስ ደህንነት ጥበቃ በአንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ ደንበኞች ልዩ የሆኑትን እንደ የጣት አሻራ እና የፊት ገጽ መለያን ያካተተ፣ የማንነት ስርቆት ተጋላጭነትን በእጅጉ የቀነሰ እና ባለ ድርብ መለያን ወደ ሥራ ያስገባ ነው፡፡

Pፍጥነት፡ ጊዜ ገንዘብ ነው! በመተግበሪያው የተካተቱት ዘመናዊ ቅንብሮች የአገልግሎት ጠያቂውን/ዋን የብድር አከፋፈል ታሪክን በፍጥነት እና በተሟላ ሁኔታ በመመዘን ለቀረበለት ብድር ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልስ የሚሰጥ ነው፡፡

Pምቹ እና በርካታ አማራጮች፡ በቀደመው የብድር አሰጣጥ ደንበኞች መበደር የሚችሉት የወርኃዊ ደመወዛቸውን እኩሌታና ሌሎች ተጨማሪ አማራጮች ያልነበሩት ሲሆን አዲሱ የአፖሎ ብድር አሠራሩን የበለጠ ለደንበኞቹ ተስማሚ በማድረግ በተለያዩ አማራጮች( በተለያዩ የመክፈያ ጊዜ ገደቦች እስከ ብር 100,000.00 ድረስ) የብድር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

Pግልጽ እና አጭር፡ ለሁሉም ደንበኞች ግልጽ የሆኑ የብድር ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶችን ያስተዋወቀው የአፖሎ የብድር መተግበሪያ ለፋይናንስ ሥርዓቱ አካታችነት ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡

ተጨማሪ ጠቃሚ ነጥቦች-ለተበዳሪዎች

  • ስለሚወስዱት ብድር ያቅዱ

ብድር ከመጠየቅዎ በፊት ስለሚወስዱት ብድር አገልግሎት( ለምሣሌ  ለቤት ዕቃ መግዣ ከሆነ የዕቃዎቹም የገበያ ዋጋ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎችዎችን ብሎም እንዴት ባለመንገድ እና መብን ያህል ጊዜ ብድሮን እንደሚመልሱ ቀድመው ይወስኑ

  • የብድር ታሪክዎን በሚገባ ይከታተሉ፡

ከላይ እንደተመለከትነው የብድር አከፋፈል ታሪክዎ በብድር ጥያቄዎ ምላሽ ላይ ያለውን አስተዋጽዖ ከግምት በማስገባት ከዚህ ቀደም የወሰዷቸውን ብድሮች አከፍፈል በሚገባ ይከታተሉ፣ በወቅቱ ክፍያ መፈጸምዎን ያረጋግጡ፡፡

  • አዳዲስ መረጃዎችን ይከታተሉ

በየወቅቱ የአፖሎ መተግበሪያ እና የአቢሲንያ ባንክ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይመልከቱ

                                     ማጠቃለያ

ተሻሽሎ የቀረበው የአፖሎ መተግበሪያ አቢሲንያ ባንክ ለደንበኞቹ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ምቹ የዲጅታል ብድር አገልግሎትን ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኛነት ያረጋገጠበት ሲሆን መተግበሪያው በፋይናንስ ዘርፍ አካታችነት ረገድ አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ተደራሽ የሚያደርግ አሠራርን በግንባር ቀደምነት ያስተዋወቀ ነው፡፡ አዲሱ የአነስተኛ ደመወዝተኞች ቅድመ ብድር በተለምዶው ብድር መጠየቅ ለከፍተኛ ነጋዴዎች እና ትልቅ ካፒታል ለሚያንቀሳቅሱ ዘርፎች ብቻ የተወሰነ የነበረውን የፋይናንስ ተቋማት የብድር ማዕቀፍ ለብዙኃኑ ቀላል እና ምቹ በሆነ አሠራር ተደራሽ ያደረገ ሲሆን ለማክሮ ኢኮኖሚውም መነቃቃት የራሱ የሆነ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡